ሮሜ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በአንደበታቸውም ሸነገሉ፤ ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” “በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም አታለዋል፤” “የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤ |
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
እጃችሁ በደም ጣታችሁም በኀጢአት ተሞልትዋል፤ ከንፈራችሁም ዐመፅን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ኀጢአትን አሰምቶአል።
እኔም ሳልናገር፦ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋርትን የተናገራችሁ፥ የሐሰት ራእይንም ያያችሁ አይደላችሁምን?”
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።