La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደን​ዛዛ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ዐይናቸው እንዳያይ፣ ጆሯቸውም እንዳይሰማ፣ እግዚአብሔር እስከዚህ ቀን ድረስ፣ የድንዛዜ መንፈስ ሰጣቸው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህም “ዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ፥ እግዚአብሔር ከባድ የእንቅልፍን መንፈስ እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው፤” ተብሎ ተጽፎአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም “እግዚአብሔር ልቡናቸውን አደነዘዘ፤ ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ በዐይናቸው አያዩም፤ በጆሮአቸውም አይሰሙም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል። ዳዊትም፦

Ver Capítulo



ሮሜ 11:8
13 Referencias Cruzadas  

እስከ ዛሬም ድረስ እንደ ልማ​ዳ​ቸው ያደ​ር​ጋሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ራሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤል ብሎ የጠ​ራ​ውን የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጆች እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ያደ​ር​ጋሉ።


እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ን​ቅ​ልፍ መን​ፈ​ስን አፍ​ስ​ሶ​ባ​ቸ​ዋል፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን፥ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ዐይን፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያዩ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ዐይን ጨፍ​ኖ​ባ​ቸ​ዋል።


እር​ሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፥ አታ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፥ አት​መ​ለ​ከ​ቱ​ምም” በላ​ቸው አለኝ።


እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው።


‘ወደ​ዚህ ሕዝብ ሂድና እን​ዲህ በላ​ቸው፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ግን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ግን አት​መ​ለ​ከ​ቱም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ ልብን፥ ታዩም ዘንድ ዐይ​ንን፥ ትሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችን እስከ ዛሬ ድረስ አል​ሰ​ጣ​ች​ሁም።