ተነሣሁ፤ ነገር ግን አላወቅሁም፥ ተመለከትሁ፥ በዐይኖቼም ፊት መልክ አልነበረም። ነገር ግን ጥላን አያለሁ፤ ድምፅንም እሰማለሁ፦
ራእይ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ግማሽ ሰዓት ያህል በሰማይ ዝምታ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ለግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ እኩል ሰዓት ያኽል በሰማይ ዝምታ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። |
ተነሣሁ፤ ነገር ግን አላወቅሁም፥ ተመለከትሁ፥ በዐይኖቼም ፊት መልክ አልነበረም። ነገር ግን ጥላን አያለሁ፤ ድምፅንም እሰማለሁ፦
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤
ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።