በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
ራእይ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያዪቱ ምድር ዐልፈዋልና፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ የፊተኛው ሰማይና የፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያይቱ ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም። |
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ ወደ ጽዮንም በደስታና በሐሤት ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ክብር በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፤ ኀዘንና ልቅሶም ይወገዳሉ።
“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ነገር ግን አስቶ በባርነት ከሚገዛው ከዚህ ወጥቶ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ አገኙአት የነጻነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው።
የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።