ራእይ 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣ በእሳት ትቃጠላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና። |
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
ትዕቢተኛ ሆይ! አንቺን የሚበቀሉበት ጊዜ፥ ቀንሽ ደርሶአልና እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሚቤዢአቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያሳርፍ ዘንድ፥ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ጠላቶቹን ወቀሳ ይወቅሳቸዋል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ረጃጅሞች በሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሕዝቡ ለከንቱ ይደክማሉ፤ አሕዛብም በመጀመሪያ በእሳት ያልቃሉ።”
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የምታስፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገለጣለች፥ መጠኗ ምንድን ነው? ማንስ ይችላታል?
ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ትልቁን ኀይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።