ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ ተንገዳግደዋል።
ራእይ 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ነገሥታት ከርሷ ጋራ አመነዘሩ፤ የምድር ነዋሪዎችም በዝሙቷ የወይን ጠጅ ሰከሩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ በዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድር ነገሥታት ከእርስዋ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ኗሪዎችም በአመንዝራነትዋ የወይን ጠጅ ሰክረዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ። |
ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ ተንገዳግደዋል።
ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።
አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውን ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቈየህ” አለው።
እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።
ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።
የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።