ራእይ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለሰባቱ መላእክት፣ “ሂዱ፤ ሰባቱን የእግዚአብሔር ቍጣ ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከቤተ መቅደሱ ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰባቱን መላእክት “ሂዱ! የእግዚአብሔርን ቊጣ የያዙትን ሰባቱን ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ!” የሚል ከፍ ያለ ድምፅ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰባቱም መላእክት፦ ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ። |
ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ ላይ መዓትህን አፍስስ።
በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “በመንኰራኵሮች መካከል በኪሩብ በታች ግባ፤ ከኪሩቤልም መካከል ከአለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ።
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።
እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኀጢኣተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።
አሁንም ሄደህ አማሌቅንና ኢያሬምን ምታ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ ከእነርሱም የምታድነው የለም። አጥፋቸው፤ መከራም አጽናባቸው፤ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያቸውም፤ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን፥ ብላቴናውንና ሕፃኑን፥ በሬውንና በጉን፥ ግመሉንና አህያውን ግደል።”