ራእይ 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ግን ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፏንም ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ምድር ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፍዋንም ከፈተችና ዘንዶው ከአፉ ተፍቶ ያፈሰሰውን ውሃ መጠጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው። |
አዛሄልም ሊገናኘው ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ከደማስቆ መልካሙን ነገር ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ወሰደ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድናለሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮኛል” አለው።