ራእይ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ መልአኩም ሄጄ “ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ፤” አልሁት። እርሱም “ውሰድና ብላት፤ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች፤” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ወደ መልአኩ ሄጄ ትንሿን ጥቅልል መጽሐፍ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፤ እርሱም፣ “ውሰድና ብላት፤ ሆድህን መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ መልአኩም ሄጄ “ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ፤” አልሁት። እርሱም “ውሰድና ብላት፤ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች፤” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ መልአኩም ሄጄ “ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ” አልኩት፤ እርሱም “ውሰድና ብላት፤ በሆድህ መራራ ትሆናለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር. ትጣፍጣለች” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ መልአኩም ሄጄ፦ ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ አልሁት። እርሱም፦ ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች አለኝ። |
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የምነግርህን ስማ፤ እንደእዚያ ዐመፀኛ ቤት ዐመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።”