Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የም​ነ​ግ​ር​ህን ስማ፤ እን​ደ​እ​ዚያ ዐመ​ፀኛ ቤት ዐመ​ፀኛ አት​ሁን፤ አፍ​ህን ክፈት፤ የም​ሰ​ጥ​ህ​ንም ብላ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፤ እኔ የምልህን ስማ፤ እንደዚያ ዐመፀኛ ቤት ዐታምፅ፤ አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፥ አፍህን ክፈት፥ የምሰጥህንም ብላ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “የሰው ልጅ ሆይ! እኔ የምነግርህን ስማ፤ አንተም እንደ እነርሱ ዐመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት፤ እኔም የምሰጥህን ብላ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፥ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 2:8
19 Referencias Cruzadas  

በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽም ጆሮ​ዬን ከፍ​ቶ​አል፤ እኔም ዐመ​ፀኛ አል​ነ​በ​ር​ሁም፤ አል​ተ​ከ​ራ​ከ​ር​ሁም።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ እን​ዲህ ተና​ገ​ረኝ፤ በዚ​ህም ሕዝብ መን​ገድ እን​ዳ​ል​ሄድ አስ​ጠ​ነ​ቀ​ቀኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂ​ያን ገዛሁ፤ ወገ​ቤ​ንም ታጠ​ቅ​ሁ​ባት።


ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም አደ​ረ​ግሁ፤ ቀን ለቀ​ንም እክ​ቴን እንደ ስደ​ተኛ እክት አወ​ጣሁ፤ በማ​ታም ጊዜ ግን​ቡን በእጄ ነደ​ልሁ፤ በጨ​ለ​ማም አወ​ጣ​ሁት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም በት​ከ​ሻዬ ላይ አን​ግቼ ተሸ​ከ​ም​ሁት።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃሌን ሁሉ በል​ብህ ጠብ​ቀው፤ በጆ​ሮ​ህም ስማው።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።


ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳ​ይህ ዘንድ አንተ ወደ​ዚህ መጥ​ተ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ እይ፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የማ​ሳ​ይ​ህ​ንም ሁሉ በል​ብህ ጠብቅ፤ የም​ታ​የ​ው​ንም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ንገር” አለኝ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።


ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።


“አሮን ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በክ​ር​ክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሰጠ​ኋት ምድር አት​ገ​ቡም።


ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ፤


ወደ መልአኩም ሄጄ “ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ፤” አልሁት። እርሱም “ውሰድና ብላት፤ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች፤” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos