በደመና ዐምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
ባሕርና ሞላዋ፥ ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ይናወጡ።
ባሕርና በውስጥዋ ያላችሁ ፍጥረቶች ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ፤ ዓለምና በእርስዋ የምትኖሩ ሁሉ ዘምሩ!
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
ምድርም ቡቃያውን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ደስታን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።