በምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ አመስግኑ፥ ደስም ይበላችሁ፥ ዘምሩም።
መብረቁ ዓለምን አበራ፤ ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች።
መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፥ ምድር አየችና ተናወጠች።
መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤ ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች።
እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል።
ምድርን ከሰማይ በታች ከመሠረቷ ያናውጣታል፥ ምሰሶዎችዋም ይንቀጠቀጣሉ።
ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ነደደ።
ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና፤
ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።
እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ “እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ
አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።