የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፥ ሥራዬንም አዩ።
ጆሮን የተከለው እርሱ አይሰማምን? ዐይንንስ የሠራ እርሱ አያይምን?
ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን?
ጆሮን የፈጠረ አምላክ አይሰማምን? ዐይንንስ የፈጠረ አምላክ አያይምን?
“ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈሮቻችን የእኛ ናቸው፥ ጌታችን ማን ነው?” የሚሉትን።
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ።
ፈተኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበቱብኝ፥ ሣቁብኝም፤ ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደንቆሮስ፥ የሚያይስ፥ ዕውርስ የሚያደርግ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።
የሚሰማ ጆሮና የሚያይ ዓይን፥ ሁለቱ የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው።
በውኑ፥ የእግዚአብሔር እጅ ማዳን አትችልምን? ጆሮውስ አይሰማምን?
አንተ አፍህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደረግህ እኔ ሰምቼአለሁ።”
አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ መስማት ከየት በተገኘ ነበር፤ አካልስ ሁሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ ማሽተት ከየት በተገኘ ነበር?