በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።
መዝሙር 91:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣን እንደ ሣር በበቀሉ ጊዜ፥ ዐመፃን የሚያደርጉም ሁሉ በለመለሙ ጊዜ፥ ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፥ ወደ አንተ የሚጠጋ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሺህ በአጠገብህ፥ ዐሥር ሺህ በስተቀኝህ ይወድቃሉ፤ አንተ ግን ከቶ አትጐዳም። |
በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።
ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ሰውነትህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በእኔ ታምነሃልና፥” ይላል እግዚአብሔር።
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመታት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።