መዝሙር 90:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራህ ለአገልጋዮችህ ይታይ፥ ግርማህም ለልጆቻቸው ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ አገልጋዮችህ ታላቁን ሥራህን እንድናይ ፍቀድልን። ልጆቻችንም የኀይልህን ክብር እንዲያዩ አድርጋቸው። |
ደግሞ፦ ይማረካሉ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ሕፃኖቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፤ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ ይወርሱአታልም።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።
“እኔም በምድር እንዳሉት ሰዎች ሁሉ ዛሬ ወደ መንገድ እሄዳለሁ፤ እናንተም አምላካችን እግዚአብሔር ስለ እኛ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ፥ በነፍሳችሁም ሁሉ ዕወቁ፤ ሁሉ ደርሶናል፤ ከእርሱም ያላገኘነው የለም።