እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።
በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር እንዲህ አስታውቀን።
ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን።
ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራቅም ማስተዋል ነው’ ” አለው።
መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰትም፥ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።
ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።
ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል አዘጋጅ።
እውነትን ግዛ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብንና ተግሣጽን፥ ማስተዋልንም።
የአፌንም ቃል ቸል አትበል።
ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።
ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ነገር ግን ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ልሠራ ይገባኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና።
ይህንም ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፤ በሚመጣውም ዘመን አያውቁትም።