መዝሙር 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የሕግ መምህርን በላያቸው ላይ ሹም፤ አሕዛብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ድንጋጤ አምጣባቸው፤ ሕዝቦች ሰው ከመሆን እንደማያልፉ ይወቁ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ተነሣ፥ ሰውም አይበርታ፥ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! እንዲፈሩህና ሰብአዊ ፍጡሮች መሆናቸውንም እንዲያውቁ አድርጋቸው። |
ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ የክንድህ ብርታትም ከድንጋይ ይልቅ ጸና፤ አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፥ የተቤዠሃቸው እኒህ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፤
በፊትህ መፈራትን እሰድዳለሁ፤ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ እንዲሸሹልህ አደርጋለሁ።
ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
ከእነርሱም እንዳልመለስ፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም።
አንተ ሰው ስትሆን ለሚገድሉህ ሰዎች፦ እግዚአብሔር ነኝ ትላቸዋለህን? ሰው ነህ እንጂ እግዚአብሔር አይደለህም።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ፤ ምስሎቹንም ከሜምፎስ እሽራለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በግብፅ ምድር አለቃ አይሆንም፤ በግብፅ ምድር ላይም ፍርሀትን አደርጋለሁ።
ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።