ማልዶ ይበቅላል ያልፋልም፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋራ ማን ሊስተካከል ይችላል? ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
አቤቱ፥ ሰማያት ድንቅ ሥራህን ታማኝነትህንም፥ በቅዱሳን ማኅበር፥ ያመሰግናሉ።
በሰማይ እግዚአብሔርን የሚመስል የለም፤ ከሰማይ መላእክትም መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚስተካከል የለም።
አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንተም ዮርዳኖስ ወደ ኋላህ የተመለስህ፥ ምን ሁናችሁ ነው?
አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።
ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ “መቼ ይሞታል? ስሙስ መቼ ይሻራል?” ይላሉ።
ሰነፍ በልቡ፦ እግዚአብሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።
ኀጢአታችንን በፊትህ አስቀመጥህ፥ ዓለማችንም በፊትህ ብርሃን ነው።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኀይል ታላቅ ነው።