“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
መዝሙር 89:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ። |
“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
ለመስማትም እንቢ አሉ፤ ያደረግህላቸውንም ተአምራት አላሰቡም፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ ለባርነታቸውም ወደ ግብፅ ይመለሱ ዘንድ አለቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓሪና ይቅር ባይ አምላክ፥ ለቍጣም የምትዘገይ፥ ምሕረትንም የምታበዛ ነህ፤ አልተውሃቸውም።
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።