አንተ ትዕቢተኛውን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኀይልህም ክንድ ጠላቶችህን በተንሃቸው።
ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን? የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ
ዐይኖቼም በመከራ ፈዘዙ፥ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
ለሙታን ተአምራትን ታደርጋለህን? እነርሱስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?
ሕያው እንድሆን ቃልህንም እንድጠብቅ ለባሪያህ ስጠው።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
ተቸግሬአለሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥ ዐይኔም ከቍጣ የተነሣ ታወከች፥ ነፍሴም፥ ሆዴም።
በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው።
ሙታን ይነሣሉ፤ በመቃብር ያሉም ይድናሉ። በምድርም የሚኖሩ ደስ ይላቸዋል፤ ከአንተ የሚገኝ ጠል መድኀኒታቸው ነውና፤ የኃጥኣንንም ምድር ታጠፋለህ።