መዝሙር 85:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህንም ለመፍራት ልቤን ደስ ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታማኝነት ከምድር በቀለች፤ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽኑ ፍቅርና እውነት ተገናኙ፥ ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ታማኝነት ከምድር ይፈልቃል ጽድቅም ከሰማይ ወደ ታች ይመለከታል። |
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
“ሰማይ በላይ ደስ ይበለው፤ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም መድኀኒትን ታብቅል፤ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ፈጥሬሃለሁ።
ነገራችን በፊቱ እንደ ሕፃን፥ በደረቅ መሬትም እንዳለ ሥር ሆነ፤ መልክና ውበት የለውም፤ እነሆ፥ አየነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ውበትም የለውም።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።