የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጠኝ።
አሦርም ከእነርሱ ጋራ ተባበረ፤ የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ
ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፥
አሦርም የሎጥን ልጆች በመርዳት ከእነርሱ ጋር ተባብራለች።
አሦርም ከዚያች ሀገር ወጣ፤ ነነዌን፥ ረሆቦት የተባለችውን ከተማ ካለህን፥
ዮቃጤንም ሶቤቅን፥ ቲማንንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች ራጉኤል፥ ንበከዝ፥ እስራኦምና ሎአም ናቸው።
በዘመኑም የአሶር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።
አቤቱ፥ ማረን፤ አንተን ተማምነናልና፤ የዐላውያን ዘራቸው ለጥፋት ነው፤ በመከራም ጊዜ መድኀኒታችን አንተ ነህ።
በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ ከአንቺም ጋር ይነግዱ ዘንድ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው በመካከልሽ ነበሩ።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።