በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰንኻቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።
የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
በአንድ ልብ በአንተ ላይ ተማከሩ፥ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፥
እነርሱም የኤዶም፥ የእስማኤል፥ የሞአብ፥ የአጋርያን፥
በሳኦልም ዘመን ከስደተኞች ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።
እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መጡ።
በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድነኛለህ፤ በጠላቶች ቍጣ ላይ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ያድነኛል
የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ።
ሞአብም በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና ሕዝብ ከመሆን ትጠፋለች።
የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፤ ሄዶም እስራኤልን መታ፤ ዘንባባ ያለባትንም ከተማ ያዘ።