የኃጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ። የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።
አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?
አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ለሁልጊዜ ያቃልላልን?
አምላክ ሆይ! ጠላቶች በአንተ ላይ የሚሳለቁት እስከ መቼ ነው? ስምህንስ የሚዳፈሩት ያለማቋረጥ ነውን?
በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።
አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይበላታል።
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።