ጠላቶችህ በበዓልህ መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።
አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።
ለሞታቸው ስቃይ የለውምና፥ ሰውነታቸውም ጤናማ ነው።
እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥ ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው።
በስብም ፊቱን ከድኖአልና ስቡንም በወገቡ ላይ አድርጎአልና፥
ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፤ በሲኦል ማረፊያም ይጋደማሉ።
ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።
በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።
ፍላጻውን ላከ፥ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
ለብልህ ከአላዋቂ ጋር ለዘለዓለም መታሰቢያ የለውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመጣልና ሁሉም ይረሳል፤ ብልህስ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል?
ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥእም በክፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከንቱ ዘመኔ አየሁ።
ፍርድን አጣመሙ ለድሃአደጎች ፍርድን አልፈረዱም፤ ለመበለቷም አልተሟገቱም።
ከዚህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ ባለጸጋውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀበረም፤