እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ።
እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።
እነሆ፥ እነዚህ ክፉዎቸ ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ሀብታቸውን ያበዛሉ።
እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው። ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።
ፍላጻውን ላከ፥ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
በሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጡ፥ የቀበሮዎችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም፥ ዘይትህንም ይበላሉ፤ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችህንም በሰይፍ ያጠፋሉ።”
ፍርድን አጣመሙ ለድሃአደጎች ፍርድን አልፈረዱም፤ ለመበለቷም አልተሟገቱም።
“አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅግም ቀጭን ልብስ ይለብስ ነበር፤ ዘወትርም ተድላና ደስታ ያደርግ ነበር።