መዝሙር 71:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጽድቅህ እስከ አርያም ይደርሳል፥ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፥ አምላክ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ጽድቅህ እስከ ሰማይ ይደርሳል፤ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ! አንተን የሚመስል ማን ነው? |
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል፥ በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ ለአንተ ክብር ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ታላቅነትህንና ኀይልህን፥ የጸናች እጅህንና የተዘረጋች ክንድህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ፥ እንደ ኀይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው?