መዝሙር 70:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላኬና መድኀኒቴ ሁነኝ፤ ኀይሌና መጠጊያዬ አንተ ነህና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ፣ “ዕሠይ! ዕሠይ!” የሚሉ፣ ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። |
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በል፦ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ ደስ ብሎሃልና፤
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰበረች፥ ጠፋችም፥ ሕዝቧም ወደ እርስዋ ተመለሱ፤ ሞልታ የነበረች አለቀች ብላለችና፤
ከዚህም በኋላ ይህ ሰው በዐመፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በምድር ላይም በግንባሩ ወደቀና ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።