“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
መዝሙር 68:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጽዮንን አድኗታልና፥ የይሁዳም ከተሞች ይሠራሉና፤ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሷታልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል። እግዚአብሔር ይባረክ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፥ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! |
“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
በዚያ ጊዜም ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለእግዚአብሔር እንዘምራለን፤ በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
የሚናገሩ ከሆነ ከጥንት ጀምሮ ይህን ምስክርነት ያደረገ ማን እንደ ሆነ በአንድነት ያውቁ ዘንድ ይቅረቡ። ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኀኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።