ሰማይና ምድር፥ ባሕርም፥ በእርስዋም የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያመሰግኑታል።
ግርማው በእስራኤል ላይ፣ ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣ እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።
በምሥራቅ በኩል በሰማየ ሰማያት ላይ ተቀምጦ ለሚጓዘው የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኀይሉም በሰማይ ላይ ስለ ሆነ የአምላክን ኀይል ዐውጁ።
እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት።
ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
እንደ ፍቁሩ አምላክ ማንም የለም፤ በሰማይ የሚኖረው፥ በጠፈርም በታላቅነት ያለው እርሱ ረዳትህ ነው።
እግዚአብሔርም ፊት ለፊት፥ በዘለዓለም ክንዶች ኀይል ይጋርድሃል፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።
ከገናናው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤” የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤
እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።