መዝሙር 68:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን እዘዝ፤ አምላክ ሆይ ቀድሞ እንዳደረግህልን አሁንም ብርታትህን አሳየን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥ ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥ የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ኀይልህን ግለጥ፤ ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ። |
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
እርሱ የጀመረላችሁን በጎውን ሥራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ እርሱ እንደሚፈጽምላችሁ አምናለሁ።
ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኀይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።
ሳኦልም መልሶ፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ ሰው አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ?” አለ።