አሁንም አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ከኀይልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረፍትህ ተነሣ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።
መዝሙር 68:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይነሣ! ጠላቶቹም ይበተኑ! የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ! |
አሁንም አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ከኀይልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረፍትህ ተነሣ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።
የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ከእነዚህ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ የዋህነት ከእኛ አልፋለችና፥ እኛም ተገሥጸናልና።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።
የሚጠሉትን ለማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፤ ለሚጠላው አይዘገይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድራትን ይመልስበታል።