መዝሙር 66:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል። አሕዛብ ደስ ይላቸዋል፥ ሐሤትም ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው! ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣ በፊትህ ይርዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ኀይልህ እጅግ ታላቅ በመሆኑ ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይሸማቀቃሉ። |
ማርያምም አስቀድማ ለእግዚአብሔር እንዘምር አለች፥ “ለእግዚአብሔር እንዘምር በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጥሎአልና።”
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ያገቡአቸዋል።
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።