በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤ የምታውቁ ራሳችሁን ከፍ ከፍ አታድርጉ።
አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣ የማዕበላቸውን ፉጨት፣ የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ በኃይልም ታጥቀሃል።
ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።
እነሆ፥ ዛሬ ጀመርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እንደሚያፈራርቅ።
ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመቅሠፍትህ አልቀናልና፤ ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ።
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
ምድርን በኀይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ ያጸና፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።
ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።
እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ ነኝ” ባላቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላቸው ተመልሰው በምድር ላይ ወደቁ።
ጲላጦስም፥ “የጻፍሁትን ጻፍሁ” ብሎ መለሰላቸው።