መዝሙር 65:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ወጥመድም አገባኸን፥ በፊታችንም መከራን አመጣህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትልምዋን ታረካለህ፥ ቦይዋንም ታስተካክላለህ፥ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥ ቡቃያዋንም ትባርካለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ቸርነት የሚገኘው መከር እንዴት ብዙ ነው! አንተ በምትገኝበት ቦታ ሁሉ ብዙ ሰብል አለ። |
የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆን በረከትን በኋላ የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከቅርንጫፎችዋ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ የዱር ወይራ የሆንህ አንተን በእነርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእነርሱንም ሥርነት አገኘህ፤ እንደ እነርሱም ዘይት ሆንኽ።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።