እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድሉታላችሁ።
አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።
ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ ከፍ ባለ ዓለት ላይ ትመራኛለህ።
አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።
እንደ ጓል በምድር ላይ ተሰነጣጠቁ እንዲሁ አጥንቶቻቸው በሲኦል ተበተኑ፥
ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት ጥበብን ትናገራለች።
ወደ እግዚአብሔር ሥራ ወደ እጆቹም ተግባር አላሰቡምና አፍርሳቸው፥ አትሥራቸውም።
ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ።
የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።
እርሱም እንዲህ ካለ ሞት አዳነን፤ ያድነንማል፤ አሁንም እንደሚያድነን እርሱን እንታመናለን።