ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤ በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።
ምሕረትህ እስከ ሰማያት ከፍ ብላለችና፤ ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች።
አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፥
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህዮችም ጥማታቸውን ያረካሉ።
በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
መንገድህን ለአግዚአብሔር ግለጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።