በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶች ወደ ኋላቸው ይመለሱ፤ አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወቅሁ።
ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።
ከዐውሎና ከብርቱ ንፋስ ሸሽቼ በፈጠንሁ አልሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! በከተማይቱ ውስጥ ዐመፅንና ብጥብጥን ስላየሁ፥ የክፉዎችን ምክር አጥፋ፤ ዕቅዳቸውንም ደምስስ!
አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም፥ “አቤቱ የአኪጦፌልን ምክር ለውጥ” አለ።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋቷ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፤ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቷ አለ።