ከኀጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
እኔ ግን ኰርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጕረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤
ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፥
እንዲሁም ከበረትህ ኰርማዎችን፥ ከጒሮኖህም አውራ ፍየሎችን ልወስድብህ አልፈልግም።
ጠላቶቼም ሁሉ ይጠቃቀሱብኛል፥ በእኔ ላይም ክፋትን ይመክራሉ።
እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌላውንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰጣልና እንደ ችግረኛ የሰው እጅ አያገለግለውም።