ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤ በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው።
የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው።
የተራራ ወፎችን ሁሉ ዐውቃቸዋለሁ በመስክ የሚገኙ እንስሶች ሁሉ የእኔ ናቸው።
ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም ፈልገው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?
እነርሱ በቍጥር እጅግ ጥቂቶችና፥ በውስጧ ስደተኞች ሲሆኑ።
ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም።
እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ ኑ፤ እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ብሉ።
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
የማይዘሩትንና የማያጭዱትን፥ ጎተራና ጕድጓድ የሌላቸውን የቍራዎችን ጫጭቶች ተመልከቱ፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል፤ እንግዲህ እናንተ ከወፎች እንዴት እጅግ አትበልጡም?