አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።
በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥ ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ጻድቃንን ትባርካለህ፤ በቸርነትህም እንደ ጋሻ መከላከያ ትሆንላቸዋለህ።
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ።
ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
ልቅሶዬን መልሰህ ደስ አሰኘኸኝ። ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ።
አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፤ ክብሬና ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
የባሕሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ በቀላዮችም መዝገቦች የሚያኖረው።
በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐመፅ የሚከብቡኝ ጠላቶቼ በረቱ፤ ያልወሰድሁትን ይከፈሉኛል።
ቅንነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተ።