ስለ መሥዋዕትህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል ቍርባንህም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤ በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤
በእውነት ማንም እራሱን አያድንም፥ ማንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
ለሰው ሕይወት የሚከፈለው ዋጋ እጅግ ብዙ ነው፤ የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
ወይስ ከጠላቶች እጅ ታስጥሉኝ ዘንድ ከኀይለኞችም እጅ ታድኑኝ ዘንድ።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?