መዝሙር 48:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአፋቸው ሲወዱ፥ ራስዋ መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣ መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤ ምሽጎችዋንም ተመልከቱ። |
እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
ከድሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎችህ ይሠራሉ፤ መሠረትህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆናል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድንም አዳሽ ትባላለህ።
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ቤት አነሣለሁ፤ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤