ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስ የሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።
እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
ጠላቶቼ ብዙ ክፉ ነገር በእኔ ላይ በመናገር “መቼ ይሞታል? መቼስ ስሙ ተረስቶ ይቀራል?” ይላሉ።
መታሰቢያውም ከምድር ይጠፋል፤ በምድርም ስም አይቀርለትም።
እነሆ ተደላድያለሁ በሚልበት ጊዜ ለዘለዓለም ይጠፋል። የሚያውቁትም ወዴት ነው? ይላሉ።
እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ጻድቅ ነው።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ።
ጻድቃን አይተው ይፍሩ፤ በእርሱም ይሳቁ እንዲህም ይበሉ፦
ወደ ልዑል እግዚአብሔር፥ ወደሚረዳኝ እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ሽንገላን ይታታሉና።
ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኃጥኣን ከአግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው።
የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።