ለድሃና ለምስኪን የሚያስብ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ከክፉ ቀን ያድነዋል።
እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።
ራሴን አዋረድሁ እንጂ። ለነፍሴ ዋጋዋን ትሰጣት ዘንድ፤ የእናቱንም ጡት እንዳስጣሉት በቃሌ ጮኽሁ።
በእኔ ላይ ተሰበሰቡ፥ ደስም አላቸው፤ ይገርፉኝ ዘንድ ተማከሩ፥ እኔ ግን አላወቅሁም። ተሰበሩ፥ አልደነገጡምም።
ነፍሴ ስድብን ጠግባለችና፥ ለሥጋዬም ድኅነትን አጣሁ።