ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። አንተ ፈጥረኸኛልና፤
ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
ዛልኩኝ እጅግም ደቀቅሁ፥ ከልቤ መጠበብ የተነሣ ጮኽሁ።
ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤ የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።
ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኀያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
ምኞትህን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጐልማስነትህን እንደ ንስር የሚያድሳት፥
በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው” አለ።
ስለ እርሱ የምንደክምለትን በሰማይ ያለውን ቤታችንን እንለብስ ዘንድ እርሱን ተስፋ እናደርጋለን።