እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
ከቂልነቴ የተነሣ፣ ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤
ዐመፃዎቼ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብለዋልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብደዋልና።
በሞኝነት ካደረግሁት ስሕተት የተነሣ ቊስሌ በስብሶ ይሸታል።
እንዲህም አልሁ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና፥ በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ፤ እፈራማለሁ።
አዲስ ምስጋናንም አመስግኑት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩለት፤
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ይሁን፥ ይሁን።
ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች።
እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፤ እግዚአብሔርም ይረዳኛል፤ ረዳቴ መጠጊያዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አምላኬ አትዘግይ።
በገለዓድ መድኀኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?