የጠላቶቼ መዘባበቻ አታድርገኝ ብያለሁና፥ እግሬም ቢሰናከል በእኔ ላይ ብዙ ነገርን ይናገራሉ።
የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።
በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።
ከክፉ ሰው ብዙ ሀብት ይልቅ፥ የደግ ሰው ጥቂት ሀብት ይበልጣል።
ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤ የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።
የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው።
የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥ በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል።
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
“ኑሮዬ ይበቃኛል፤” ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤