መዝሙር 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባሕሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ በቀላዮችም መዝገቦች የሚያኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ በድል ዝማሬም ትከብበኛለህ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጭንቅ ትጠብቀኛለህ፥ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ ስላዳንከኝ በከፍተኛ ድምፅ በደስታ እዘምራለሁ። |
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
ንጉሡም ጸሓፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፤ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው።