መዝሙር 32:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀንና በሌሊት፣ እጅህ ከብዳብኛለችና፤ ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደ ላሰው ነገር፣ ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ ጉልበቴ በበጋ ትኩሳት ዛለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤ ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ ጒልበቴ በፍጹም አለቀ። |
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል።
እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፣ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ” አሉ።
ከሄደችም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ታላቁንም ታናሹንም መታ፤ የውስጥ አካላቸውንም በእባጭ መታቸው፤ የጌት ሰዎችም የውስጥ አካላቸውን ምስል ሠሩ፥
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”